ለሁሉም በተለይም ለ2012 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች
ማስታወሻ፣
እናምናለን በኮረና ቫይረስ ምክንያት የደበዘዘዉ ቀናችን ጊዜው ስደርስ መንጋቱ አይቀርም። ስለዚህ ህይወት  ይቀጥላል፣ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴም ወደ ቦታው ይመለሳል።
ስለዚህ ዉድ ተማሪዎቻችንን የሚከተሉትን ነጥቦች ማስታወስ እንወዳለን፣
1. 60% ተከታታይ ምዘና እና 40% ማጠቃለያ ምዘና የሚሰጡ በኘሮጀክት መሆኑን አዉቃችሁ በኦንላይን የተላኩላችሁን ኮርስ ማቴሪያሎች፣ የሚነበቡ መጵሐፍት እና ማጣቀሻ ዎችን ተግታችሁ አንብቡ።
2. ዓመታዊ የት/ት ሰሌዳ ምረቃን ጨምሮ የማይቀር መሆኑን ተገንዝባችሁ የሚጠበቅባችሁን በተቀመጠው ጊዜ ዉስጥ አጠናቅቁ፤ በተለይ የማስተርስ ተመራማሪዎች የምረቃ ጽሑፋችሁን በርትታችሁ  ቀጥሉበት እንላለን።
3. ሁሉም ተማሪዎቻችን የርቀትንም ጨምሮ ከካምፓሶቻችሁ ጋር በኦንላይን የጠበቀ ግኑኝነት በማድረግ በየጊዜው የሚሰጡ መመሪያዎችን እንድትከታተሉ እናሳስባለን።
ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ
ስላም እንመኝላችሃለን።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here